1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ለመሆን የጠየቀችዉ ጎራ ለማማረጥ አይደለም-ዉጉሚ

ዓርብ፣ ነሐሴ 19 2015

ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ብሪክስን በአባልነት ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በተሰየመዉ የብሪክስ ጉባኤ ጥያቄዋ ተቀባይነት ማግኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝርዝር ማብራሪያ ባይሰጡበትም ይህ ለኢትዮጵያ "ታሪካዊ ሁነት" ነው ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4VXy3
የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ መለስ ዓለም መግለጫ ሲሰጡ
የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ መለስ ዓለም መግለጫ ሲሰጡምስል Solomon Muchie/DW

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆንዋ፣ የስደተኞች መገደልና የርዳታ መቋረጥ

ኢትዮጵያ BRICS የተባለው ማሕበር አባል ለመሆን የጠየቀችዉ ከተለያዩ ወገኖች አንዱን ለመምረጥ እንዳልሆነ የሐገሪቱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።ዛሬ መግለጫ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ስለዚሁ ጉዳይ ተጠይቀው ኢትዮጵያ ይህንን ስብስብ ለመቀላቀል ጥያቄ ያቀረበችው "አንዱን ጎራ ትቶ አንዱን የመያዝ ፍላጎት ስላላት አይደለም" ብለዋል። ቃል ዐቀባዩ የሳዑዲ ዓረብያ ወታደሮች በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የተፈፀመውን ግድያ በተመለከተ መንግሥት ከዚህ በፊት ጉዳዩን እየተከታተለ ነው በሚል ከሰጠው የተለየ ተጣርቶ የቀረበ መረጃ አለመኖሩን ገልፀዋል። ሰለሞን ሙጬ ጋዜጣዊo መግለጫዉን ተከታትሎታል።

 

                የምሥራቅ ወይም የምዕራብ ጎራ መለየት አይደለም

ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ብሪክስን በአባልነት ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በተሰየመዉ የብሪክስ ጉባኤ ጥያቄዋ ተቀባይነት ማግኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝርዝር ማብራሪያ ባይሰጡበትም ይህ ለኢትዮጵያ "ታሪካዊ ሁነት" ነው ብለዋል።የብሪክስ ጉባኤ በጁሐንስበርግ-ደቡብ አፍሪቃ

ዛሬ መግለጫ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ይህ የኢትዮጵያ ጥያቄ ዓለም ላይ ካሉ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጎራ የለዩ መሰባሰቦች የምስራቅ ወይም የምዕራብ የሚል ጎራ የመፈለግ አዝማሚያ አይደለምን ተብለው ተጠይቀዋል።

የብሪክስ ጉባኤ አርማ
የብሪክስ ጉባኤ አርማ ምስል Sergei Bobylev/TASS/dpa/picture alliance

"የዚህኛውም ተሳትፎዋ አንዱን ጎራ ትቶ ሌላ ጎራ የመፈለግ ተደርጎ በጋዜጠኞች ሲቀርብ ይታያል። ይህ ስህተት ነው። ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማሲዋ የሚታወቀው በገምቢ ገለልተኛነት ነው። በዚህ መድረክ ላይ የምትሳተፈው በአለም አቀፍ መድረኮች በሁለትዮሽ ብቻ ሳይሆን የባለ ብዙ ወገን መድረኮች አራማጅ ናት"

 

                     የኢትዮጵያዊያን ሞት በሳውዲ ፣ የመንግሥት ምላሽ

ኢትዮጵያ በዋናነት በሕገ ወጥ ስደት ባህር ተሻግረው የሚጓዙ እና በቤት ውስጥ ሥራ የሚሰማሩ እስከ 750,000 የሚጠጉ ዜጎቿ በሳውዲ አረቢያ ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል።

ኢትዮጵያ በቅርቡ ከ 100 ሺህ በላይ ዜጎቿን ከዚህችው ሀገር ሳውዲ አረቢያ መልሳለች።

ሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉን ተመላሾች
ሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉን ተመላሾች ምስል EDUARDO SOTERAS/AFP

የሳውዲ አረቢያ የድንበር ጠባቂዎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ምናልባትም በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በጥይት መግደላቸውን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች ሰሞኑን በምስል አስደግፎ አጋልጧል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን በተመለከተ ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ ጉዳዩን እየተከታተለ መሆኑን እና ከሳውዲ መንግሥት ጋር በመሆን በአስቸኳይ የተፈፀመውን እንደሚያጣራ እና እንደሚያሳውቅ ገልጾ ነበር።አምባሳደር መለስ አለም ከዚህ የተለየ መልስ እንደሌላቸው ገልፀዋል።የሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች ኢትዮጵያዉያንን ገደሉ

"ይህ አሳዛኝ ተግባር ነው። ጉዳዩ በማንም ተፈፀመ፣ የትም አሳዛኝ ተግባር በመሆኑ ሊወገዝ ይገባል። ከዚያ ውጪ የኢትዮጵያ መንግሥት ጉዳዩን ያጣራል የሚል የመጨረሻ መግለጫ አውጥቷል። እስካሁን በደንብ ተጣርቶ የተገኘ ነገር የለም ብለዋል።

 

                                              የኢትዮጵያ የቀጣይ የዲፕሎማዲ አቅጣጫ፣ የውስሕ ግጭት ፈተና

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በ2016 ዓ. ም የላቀ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን መፍጠር እና በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረ የግንኙነት መሻከር የስከተለውን ችግር በመቅረፍ አጋሮችን የማብዛት ሥራ ላይ እንደሚያተኩር ቃል ዐቀባዩ ገልፀዋል።

በሌላ በከል ዩናይትድ ስቴትስ እና አጋሮቿ በአንድ በኩል፣ የአውሮጳ ሕብረት ተልዕኮ በኢትዮጵያ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭት እንዳሳሰባቸው በቅርቡ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በየመንና ሳዑዲ አረቢያ ድንበር
ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በየመንና ሳዑዲ አረቢያ ድንበር ምስል Khaled Abdullah/REUTERS

ይህ ጦርነት ለሌላ የግንኙነት መሻከር ምክንያት አይሆንም ወይ ? ከያዛችሁት የውጭ ግንኙነት አቅጣጫ ጋርስ አይጋጭምን ? በሚል የተጠየቁት አምባሳደር መለስ ውጭ ጉዳይ ግንኙነትን ማሻሻል ላይ እንደሚያተኩሩ በመግለጽ ጦርነቱን በተመልከተ ምንም መናገር እንደማይችሉ ገልፀዋል።ኢትዮጵያዉን በወገኖቻቸዉ የሚደርስባቸዉ በደል በሳዑዲ አረቢያ

 

                          በትግራይ የእርዳታ እህል መዘረፍ እና ያስነሳው ጥያቄ

በትግራይ ክልል ዘረፋ ስለተፈፀመበት የእርዳታ እህል፣ ይህንንም ተከትሎ ድጋፍ ስላቆሙ ረጂ ድርጅቶች ወቅታዊ ሁኔታም ማብራሪያ ተጠይቀዋል።

" የምግብ መወሰድ ጋር በተያያዘ የእርዳታ ተግባር ያቆሙ አካላት አሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት ተጠያቂነት እንዲኖር ይፈልጋል። በዚህ ተግባር ላይ ያሉ ሰዎች እንዲጠየቁ የምርመራ ሥራ እየተሰራ ይገኛል"

ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ