1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድርድሩና የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 26 2014

«ድርድሩ ያስፈልጋል ጦርነቱ አያስፈልግም ነበር ያም ሆኖ ድርድር የሚደረግ ከሆነ ሁሉም የትግራይ ህዝብ መሳተፍ አለበት» ተቃዋሚው ባይቶና ፓርቲ

https://p.dw.com/p/4F2AW
Äthiopien | Addis Abeba Olusegun Obasanjo

ስለ መንግሥትና ህወሓት ድርድር የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ከሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) አመራሮች ጋር የሚደረጉ ድርድሮች በሙሉ በአፍሪካ ኅብረት መሪነት ብቻ መካሄድ እንዳለባቸው አስታውቋል።ከዚህ ቀደም ሁለቱን ወገኖች በተናጠል ሲያነጋግሩ የነበሩት የአፍሪቃ ኅብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆን ለኢትዮጵያ ይወግናሉ ያለው ህውሓት ንግግሩ በኬንያው መሪ ኡሁሩ ኬንያታ አስተባባሪነት እንዲመራ እንደሚፈልግ ተናግሯል።በሌላ በኩል የፌደራሉ መንግሥት ከትግራይ ኃይሎች ጋር በየትኛውም ስፍራ፣ በማንኛውም ጊዜ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ  አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓም መናገራቸውን ይታወሳል። የህወሓት ሊቀመንበር ዶ\ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል ደግሞ ፣ የትግራይ ሠራዊት ትጥቅ መፍታት ጉዳይ ለድርድር እንደማይቀርብ ፣ከድርድሩ በፊት መሰረታዊ አገልግሎቶች ማለትም የስልክ፣ የባንክ ፣የኤሌክትሪክና የመሳሰሉት አገልግሎቶች በሙሉ እንዲጀመሩ ፣ በጦርነት የደረሱ ጉዳቶች በገለልተኛ ወገን ተጣርተው አጥፊዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ምዕራብና ምሥራቅ ትግራይ አሉ ያሏቸው የኤርትራ ሠራዊትና የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ከአካባቢው እንዲወጡ ሲሉ ሐምሌ 20 ፣ 2014 ዓም በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። በነዚህ ጉዳዮች ላይ የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? ስለ ድርድሩ ያላቸው አቋምስ ምንድን ነው? ሦስት የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ማለትም የባይቶና ፤ሳልስይ ወያነ እና የአረና ትግራይ ፓርቲ አመራሮችን አስተያየት ጠይቀናል። ተቃዋሚው ባይቶና ፓርቲ ድርድሩ የትግራይን ህዝብ መሳተፍ አለበት ባይ ነው። የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል  አቶ ዩሴፍ ኃይለ ስላሴ። 
 «ምንድነው የሚስማሙት የሚለው ነገር እራሱ አናውቀውም  ድርድሩ ብዙ ውጤት ይኖረዋል ብለን አይታየንም ቢኖር እንኳን ህውሓት ብቻውን ሊሰራው አይችልም የሚል አቋም ነው ያለን ።ድርድሩ ያስፈልጋል ጦርነቱ አያስፈልግም ነበር ያም ሆኖ አሁን የሚደራደሩት በምን ላይ እንደሆነ ድርድር የሚደረግ ከሆነ ሁሉም የትግራይ ህዝብ መሳተፍ አለበት» 
የአረና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት  አቶ ጎይቶም ፀጋዬ በትግራይ መሠረታዊ አገልግሎቶች መሟላት አለባቸው ይላሉ። 
«እንደቅድመ ሁኔታ መሟላት ያለባቸው ነገሮች አሉ የባንክ አገልግሎት የመብራት አ,ልግሎት ,፣የትራንስፖርት አገልግሎት እና እርዳታ እና የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቃያቸው የመመለሳ ጉዳይ የህውሓት ጉዳይም አይደል የብልፅግና ጉዳይም አይደል ሀላፊነታቸው እንደሆነ አምነው ልክ እንደሌላው የኢትዩጵያ ህዝብ ግልጋሎት ማግኘት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መደረግ አለበት ።»
የሳልስይ ወያነ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሀይሉ ከበደ በበኩላቸው ከድርድሩ በፊት በተለያዩ ክልሎች የታሰሩ የትግራይ ተወላጆች እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
«በሰላም እናጠናቅቃለን ማለታቸው የሚበረታታ ተግባር ነው ጦርነቱ መጀመሪያ አይጠቅምም ነው ስንል የነበረው መጀመሪያ ፍላጎት መኖር አለበት በሁሉም ክልልሎች የታሰሩ የትግራይ ተወላጆች መፈታት አለባቸው »

Äthiopien | Unruhen | Redwan Hussein, ein Sprecher des Amtes des Premierministers
ምስል Minasse Wondimu Hailu/AA/picture alliance

ማኅሌት ፋሲል
ኂሩት መለሰ