1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚኢትዮጵያ

የትግራይ ምሁራን ፍልሰት

ሐሙስ፣ መስከረም 10 2016

በትግራይ ትልቁ ከሆነው ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ብቻ ከ180 በላይ ዶክተሮች እና ሌሎች በማከም እና የሕክምና ሙያ በማስተማር ላይ የነበሩ ምሁራን በተወሰነ ግዜ ብቻ መልቀቃቸው ተገልጿል

https://p.dw.com/p/4Wetj
በ2 ዓመት ብቻ ከዓይደር ሆስፒታል ከ180 በላይ ባለሙያዎች ተሰድደዋል
በቀሌ ዩኚቨርስቲ የዓይደር ሆስፒታል ምስል Million Hailessilasie/DW

ከዐይደር ሆስፒታል ብቻ 180 ሐኪሞች ለቅቀዋል

ትግራይ ዉስጥ ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ ወዲሕ በክልሉ የነበሩ  ምሁራንና ባለሙያዎች ክልሉን ለቀው እየተሰደዱ መሆኑ ተነገረ። በተለይም የጤና ባለሙያዎች በተለያዩ ከክልሉ ለቀው እየወጡ መሆኑ የሚነገር ሲሆን በመቐለ ከሚገኘው ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ብቻ በሁለት ዓመት ዉስጥ ከ180 በላይ የጤና ባለሙያዎች መልቀቃቸው ተተዘግቧል።ለምሁራኑ እና ባለሙያዎቹ መልቀቅ ኢኮኖሚያዊ እና ሌሎች ምክንያቶች በቀዳሚነት ተጠቅሰዋል።ስርቆት፣ ዘረፋ፣ እገታና ሥርዓተ አልበኝነት በትግራይ

በትግራይ ከጦርነቱ ጅማሮ በኃላ ባለው ግዜ በስፋት እየተስተዋሉ ካሉ አጋጣሚዎች መካከል አንዱ፥ በተለያዩ ዘርፎች ይሰሩ፣ ያስተምሩ፣ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ምሁራን እና ባለሙያዎች ክልሉን ለቆ ወደተለያየ የኢትዮጵያ አካባቢ አልያም ውጭ ሀገራት መሄድ ይስተዋላል። በተለይም ሐኪሞች፣ የተለያየ ደረጃ አስተማሪዎች፣ መሀንዲሶች እና ሌሎች ምሁራንና ባለሙያዎች ከጦርነቱ መጀመር በኃላ ባለው ግዜ በስፋት ከትግራይ የሚለቁበት ሁኔታ እንደሚታይ መረጃዎች ያመለክታሉ። የድህንነት ስጋቶች፣ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፣ አመቺ የስራ ሁኔታ አለመፈጠር፣ እንቅስቃሴ መቀዛቀዝ እና ሌሎች ገፊ እና በሌላ አካባቢ ያሉ ሳቢ ምክንያቶች ምሁራኑ እና ባለሙያዎቹ ከትግራይ ለቀው እንዲሄዱ እንደሚያደርጉ ተነግሯል። በትግራይ ትልቁ ከሆነው ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ብቻ ከ180 በላይ ዶክተሮች እና ሌሎች በማከም እና የሕክምና ሙያ በማስተማር ላይ የነበሩ ምሁራን በተወሰነ ግዜ ብቻ መልቀቃቸው ተገልጿል። በመቐለ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአካዳሚክ እና ምርምር ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር አብርሃ ገብረሰላማ ለዶቼቬለ እንደገለፁት በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ስር ከሚተዳደረው ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በሁለት ዓመት ውስጥ ከለቀቁ ከ180 በላይ የጤና ባለሙያዎች መካከል በርካታ ስፔሻላይዝ ያደረጉ ዶክተሮች፣  ጠቅላይ ሕመሞች እና ሌሎች ተፈላጊ የሚባሉ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ዜግነት ያላቸው ባለሙያዎች እንደሚገኙ አንስተዋል።ተፈናቃዮችና አዲስ ዓመት በመቐለ

የዓይደር ሆስፒታል
የዓይደር ሆስፒታል የሕክምና ባለሙያዎች በሥልጠና ላይምስል Yasuyoshi Chiba/AFP/Getty Images

ይህ በብዛት የሐኪሞች መልቀቅም በትግራይ ተመሰቃቅሎ ያለው የጤና አገልግሎት ስርዓት ይበልጥ ያወሳሰበ መሆኑ ተመልክቷል። ከዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ውጭ፣ ከሌሎች በርካታ በትግራይ የሚገኙ የሕክምና ተቋማትም ጥቂት የማይባሉ ዶክተሮች እና ሌሎች የሕክምና ባለሙያዎች እየለቀቁ ወደ ሌላ የሀገሪቱ ክፍል ይሄዳሉ፣ ከሀገር ይወጣሉ አልያም በሌላ ዘርፍ ተሰማርተው ሲሰሩ ይተስተዋላል። እንደነ ሶማሌላንድ፣ ሶማልያ እና ደቡብ ሱዳን የመሳሰሉ ሀገራት ደግሞ እነዚህ ከትግራይ ጨምሮ በአጠቃላይ ከሀገሪቱ ለቀው የሚሄዱ ሐኪሞች መዳረሻ እየሆኑ እንዳሉ ከባለሙያዎቹ ሰምተናል። በክልሉ ካለ አንድ የመንግስት ሆስፒታል ለቃ ወደሌላ የገባች አንድ ስሟ እንዲገለፅ ያልፈለገች ሜዲካል ዶክተር፥ እርሷ ጨምሮ በርካቶች በተለያዩ ገፊ ምክንያቶች ትግራይን እየለቀቁ መሆኑ ገልፃልናለች። "ለሶስት ዓመታት ሐኪሞች በነፃ ነበር ሲያገለግሉ የነበሩት፥ አሁንም ቢሆን ለአገልግሎቱ ያገኘው ካሳ የለም። ለሐኪሞች የተነገረ ነገር ቢኖር አሁንም መጪው ግዜ አሳሳቢ መሆኑ እና በቂ በጀት እንደሌለ ነው። ስለዚህ ሐኪምም እንደሌላው የራሱ ኑሮ፣ ቤተሰብ ስላለው ሳይወድ ሌላ አማራጭ እንዲያይ እያደረገው ይገኛል። በአካባቢያችን ደግሞ እንደነ ሶማሊላንድ፣ ሶማልያ፣ ደቡብ ሱዳን የመሳሰሉ በብዙ እጥፍ የተሻለ ደሞዝ ለሐኪሞች ይከፍላሉ። ስለዚህ የኢኮኖሚ ጉዳይ አንዱ ገፊ ምክንያት ነው" ትላለች።የ33 የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች እና የሲቪል ማሕበራት ተቃውሞ

ከኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች በተጨማሪ በትግራይ ያለ አጠቃላይ ሁኔታ ሐኪሞች ጨምሮ ሌሎች ባለሙያዎች እንዲሰደዱ እያደረገ መሆኑ ተነግሯል።

የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ብዙ ምሑራን እየተሰደዱበት ነዉ
የመቀሌ ዩኒቨርስቲ አርማ

በተለይም ሐኪሞ ከተለያዩ የትግራይ የጤና ተቋማት በስፋት መልቀቅ ጉዳይ ከትግራይ ጤና ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለግዜው አልተሳካም። በትግራይ ከጦርነቱ ጀማሮ በኃላ ባለው ግዜ የመንግስት ሰራተኞች የሚጠብቁት ደሞዝ ለረዥም ግዜ ያላገኙ ሲሆን በዚህም በርካቶች በተገኘ ዕድል ለመሰደድ እንዲሁም ዘርፍ ለመቀየር እንደገፋቸው ይገልፃሉ።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ