1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮቪድ ህግጋቶች ይነሱ ተቃዉሞ በቻይና

ሰኞ፣ ኅዳር 19 2015

በሳምንቱ መጨረሻ በቻይና በርካታ ከተሞች የተቀሰቀሰዉ ከፍተኛ ተቃዉሞ እስከ ሰኞ ምሽት ድረስ መቀጠሉ ተነግሯል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች በዋና ከተማዋ ቤጂንግ በተለይ ዲፕሎማቶች በሚገኙበት አካባቢ ማታ ማታ የሚወጡ ሰልፈኞች ላይ እርምጃ መዉሰዳቸዉ ተሰምቷል ።

https://p.dw.com/p/4KCar
China | Coronavirus - Protest in Peking gegen die Null-Covid-Politik
ምስል Koki Kataoka/Yomiuri Shimbun/AP Photo/picture alliance

በቻይና ባለፉት አሥርተ ዓመታት ውስጥ ያልታየ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ተቀስቅሶ በርካታ ሰዎች ታሰሩ። ህዝባዊ ተቃዉሞዉ ሃገሪቱ የያዘችዉ ኮሮናን ሙሉ በሙሉ የማጥፋት ፖለቲካ፤ ህዝቡ በየጊዜዉ ለምርመራ በመጠራቱ፤ የዝዉዉር እግድን ጨምሮ  የኮሮና መከላከያ ጥብቅ ህጎች ተግባራዊ ማድረግን ብሎም ተገልሎ መቀመጥ ህግ ሰለቸን በማለቱ ነዉ።  በሳምንቱ መጨረሻ በቻይና በርካታ ከተሞች የተቀሰቀሰዉ ከፍተኛ ተቃዉሞ እስከ ሰኞ ምሽት ድረስ መቀጠሉ ተነግሯል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች በዋና ከተማዋ ቤጂንግ በተለይ ዲፕሎማቶች በሚገኙበት አካባቢ ማታ ማታ የሚወጡ ሰልፈኞች ላይ እርምጃ መዉሰዳቸዉ ተሰምቷል ።

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ