1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 ፊቼ ጫምበላላ

ዓርብ፣ ግንቦት 23 2011

የሐገር ሽማግሌዎች በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሲዳማ ዞን የክልል መስተዳድርነት ሥልጣን እንዲኖረዉ ከዚሕ ቀደም የተወሰነዉ ገቢር እንዲሆን ጠይቀዋል።ባለፈው ዓመት የፊቼ - ጫምባላላ በዓል ሲከበር  በተቀሰቀሰ ግጭት የሰው ሕይወትና ንብረት ጠፍቶ ነበር

https://p.dw.com/p/3JZXC
Äthiopien Hawassa - Fichee-Chambalaalla Fest
ምስል DW/S. Wegayehu

ፊቼ ጫምበላላ

የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ - ጫምባላላ ዛሬ ሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ በሚገኘው አደባባይ (ጉዱማሌ) እየተከበረ ነዉ።በበዓሉ ላይ በሲዳማ ዞን ከሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የተዉጣጣ በሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ፤የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የፌደራልና የአጎራባች ክልሎች ባለሥልጣናት ተካፍለዋል።የሐገር ሽማግሌዎች በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሲዳማ ዞን የክልል መስተዳድርነት ሥልጣን እንዲኖረዉ ከዚሕ ቀደም የተወሰነዉ ገቢር እንዲሆን ጠይቀዋል።ባለፈው ዓመት የፊቼ - ጫምባላላ በዓል ሲከበር  በተቀሰቀሰ ግጭት የሰው ሕይወትና ንብረት ጠፍቶ ነበር።የሐዋሳዉ ዘጋቢያችን ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ እንዳለዉ የዘንድሮዉ በዓል ከዋዜማዉ ጀምሮ ሠላማዊ ነበር።የግጭት ሥጋት ግን አልተለየዉም።

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ

ነጋሽ መሐመድ 

ሸዋዬ ለገሰ