1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አብን አባላት እና ደጋፊዎቹ መታሠራቸውን ማመልከተ

ዓርብ፣ ሰኔ 21 2011

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ( አብን ) ተሞከረ ከተባለው መፈንቅለ መንግስት ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልል ከ 100 በላይ የፖርቲው አባላትና አባል ያልሆኑ ሰዎች መታሰራቸውን ይፋ አደረገ።

https://p.dw.com/p/3LCUw
Karte Äthiopien englisch

ከመቶ በላይ ታስረዋል፤ አብን

የፖርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ እንዳሉት ግለሰቦቹ እየተያዙ ያሉት መፈንቅለ መንግስቱን በማቀናበር አብን አለበት በሚልና ፣ የገንዘብ ድጋፍ ታደርጋላችሁ በሚል መታሰራቸውን ፤ አንዳንዶቹም የት እንደታሰሩ እንደማይታወቅ ተናግረዋል።
ጉዳዩ ህዝብን ወደ አለመረጋጋት፣ ሀገሪቱንም ወደባሰ ሁኔታ የሚያስገባ በመሆኑ ድርጊቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ፣ የተያዙትም እንዲለቀቁ ጠይቋል። ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ጉዳዩን ለህዝብ በማሳወቅ ህዝቡ በመንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድር እናደርጋለን ሲሉ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ለ DW ተናግረዋል። መንግሥት ከዚሁ የመፈንቅለ መንግሥት ተግባር ካለው ጉዳይ ጋር በተያያዘ ትናንት  ስድስት ሰዎችን በሽብር ከስሶ ፍርድ ቤት ማቅረቡን መዘገባችን ይታወሳል። ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዘገባ ልኮልናል።

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ