1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

ትራምፕ ወይስ ባይደን? ትውልደ ኢትዮጵያውያን ማንን ለምን ይመርጣሉ?

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 21 2013

ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዶናልድ ትራምፕ እና መንግሥታቸው በአሜሪካ የጤና መድኅን ዋስትና ላይ የሚከተሉት አቋም፤ የኢሚግሬሽን ቪዛ ሎተሪን ለማቆም የጀመሩት ጥረት እና ለጥቁር ዜጎች ያላቸው አመለካከት ጆ ባይደንን እንዲመርጡ እንደሚያደርጓቸው ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ትራምፕ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ላይ የሰጡት አስተያየትም ከፍ ያለ ሚና ይጫወታል

https://p.dw.com/p/3kh3V
Donald Trump und Joe Biden
ምስል Patrick Semansky/AP Photo/picture-alliance

ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ምርጫ

ከሁለት ቀናት በኋላ በሚደረገው የአሜሪካ ምርጫ ግብጽ የኢትዮጵያን ግድብ "ታፈነዳለች" ያሉት ዶናልድ ትራምፕ ለሚቀጥሉት አራት አመታት የልዕለ ኃያሏ አገር ፕሬዝዳንት ሆነው የመቀጠላቸው ነገር ይለይለታል። የ74 አመቱ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት የሰጡት አስተያየት ሊመርጧቸው የተዘጋጁ ኢትዮጵያውያን ጭምር አሽሽቶባቸዋል።

በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በምርጫው ድምጽ ሲሰጡ ከግድቡ ጉዳይ ባሻገር ወደ ዴሞክራቲክ ፓርቲ እጩ ጆ ባይደን እንዲያጋድሉ የሚያስገድዷቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ።

ዶናልድ ትራምፕ እና መንግሥታቸው በአገሪቱ የጤና መድኅን ዋስትና ላይ የሚከተሉት አቋም፤ የኢሚግሬሽን ቪዛ ሎተሪን ለማቆም የጀመሩት ጥረት እና ለጥቁር ዜጎች ያላቸው አመለካከት ጆ ባይደንን እንዲመርጡ እንደሚያደርጓቸው ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

አሜሪካውያን ከሁለቱ እጩዎች አንዱን ለመምረጥ ድምጻቸውን በመጪው ማክሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ይሰጣሉ። ይሁንና እስከ ዛሬ ድረስ ከ80 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን ከምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት አሊያም በፖስታ በመላክ ድምጽ ሰጥተዋል።

ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የዶይቼ ቬለ ወኪል አበበ ፈለቀ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድምጽ ሲሰጡ ትራምፕ እና ባይደንን በየትኞቹ ፖሊሲዎች እንደሚመዝኗቸው ጠይቆ ነበር።  

አበበ ፈለቀ

እሸቴ በቀለ  

#የአሜሪካ_ምርጫ_2020