1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የጀርመን ጥምር መንግስት

ረቡዕ፣ ኅዳር 29 2014

የሶሻል ዴሞክራቶች፣የአረንጓዴዎቹና የነፃ ወይም የሊብራሎቹ ፓርቲዎች መንግስት የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭትን መግታትና የሐገሪቱን ምጣኔ ሐብት ማሳደግን ጨምሮ ጀርመንና አዉሮጳን በቅጡ የመምራት ኃላፊነት ተጥሎበታል

https://p.dw.com/p/43zpD
Deutschland Merkel übergibt Kanzleramt an Scholz
ምስል Markus Schreiber/AP Photo/picture alliance

አዲሱ የጀርመን ተጣማሪ መንግስት ዓላማና ኃላፊነት

ባለፈዉ መስከረም ጀርመን ዉስጥ በተደረገዉ አጠቃላይ ምርጫ የተሻለ ድምፅ ያገኙት ሶስቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመመሠረቱት ተጣማሪ መንግስት ዛሬ በይፋ ሥራ ጀምሯል።ጀርመን ለጥምር መንግስት እንግዳ ባትሆንም ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ያጣመረ መንግስት ሲመሠረትባት ያሁኑ የመጀመሪያዋ ነዉ።የሶሻል ዴሞክራቶች፣የአረንጓዴዎቹና የነፃ ወይም የሊብራሎቹ ፓርቲዎች መንግስት የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭትን መግታትና የሐገሪቱን ምጣኔ ሐብት ማሳደግን ጨምሮ ጀርመንና አዉሮጳን በቅጡ የመምራት ኃላፊነት ተጥሎበታል።ታዛቢዎች እንደሚሉት ዛሬ የመራሔ መንግስትነቱን ሥልጣን የተረከቡት ኦላፍ ሾልስም ላለፉት 16 ዓመታት ሐገሪቱን የመሩትን የአንጌላ ሜርክልን ምግባር፣ስምና ዝናን ለመተካት አበክረዉ መታተር ይጠበቅባቸዋል።

 ይልማ ኃይለ ሚካኤል 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ