1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግማሽ ሚሊዮን በተፈናቀለባት ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 1 ሚሊዮን ኼክታር መሬት ሊለማ ነው ተባለ

ዓርብ፣ ግንቦት 19 2014

ግማሽ ሚሊዮን ነዋሪዎች በተፈናቀሉበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በዘንድሮ ክረምት ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ሄክታር መሬት በምርት ለመሸፈን መታቀዱን የክልሉ ግብርና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት ዐአስታወቀ። እስካሁን 60ሺ ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ጽ/ቤት ኃለፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናግረዋል፡

https://p.dw.com/p/4BxKE
Äthiopien Vertreibung und Massaker in der Region West-Benishangul Gumuz
ምስል Maria Gerth-Niculescu/DW

እስካሁን 60ሺ ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ጽ/ቤት ገልጧል

ግማሽ ሚሊዮን ነዋሪዎች በተፈናቀሉበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በዘንድሮ ክረምት ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ሄክታር መሬት በምርት ለመሸፈን መታቀዱን የክልሉ ግብርና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት ዐስታወቀ።  እስካሁን 60ሺ ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ጽ/ቤት ኃለፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናግረዋል፡፡ ወደ ተግባር እንደገቡ ከተነገረላቸው  ወረዳዎች ብዛት አንጻር በዚህ ዓመት የተሻለ ምርት ይገኛል የሚል ግምት እንዳላቸውም ኃላፊው ጠቁመዋል። አርሶ አደሮች በበኩላቸው፦ የተለያዩ የግብአት እጥረት እንደገጠማቸው ተናግረዋል። የግብአት እጥረት እንደ ሀገር ያጋጠሙ ችግሮች መሆናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል። በሁለት ወረዳዎች ውስጥ የተምች ጥቃት መከሰቱንና የተመች መከላከያ ኬሚካል ለመላክ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። 

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የምርት እጥረትን ለመቀነስና የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት በበጋ ወራት ከተሰሩት የመስኖ ምርት 4 ሚሊዩን ኩንታል መሰብሰቡን የክልሉ ግብርና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ አመልክተዋል፡፡ በበክረምት መደበኛ የምርት ወራት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሄክታር መሬት በምርት ለመሸፈን በክልሉ የተለያዩ ስፍራዎች ወደ ስራ መገባቱን የቢሮው ኃላፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ አብራርተዋል፡፡ በዘንድሮ ክምረት በምርት ለመሸፈን የታቀደው መሬት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸርም ከአነድ መቶ ሺ ሄክታል በላይ ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡ በክልሉ አሶሳ ዞን የተወሰኑ ወረዳዎች የእርሻ መሳሪያዎች ለአርሶ አደሩ በተቋሙ በኩል መቅረቡን ተናግረዋል፡፡  

Äthiopien Vertreibung und Massaker in der Region West-Benishangul Gumuz
ምስል Maria Gerth-Niculescu/DW

በክልሉ በጸጥታ ችግር ምክንያት በየመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ወደ ቀድሞ ቀዬአቸው ባለ መመለሳቸው ወደ ሥራ አለመግባታቸውን ገልጸዋል፡፡ በርካታ አርሶ አደሮች ለእርሻ ምርት የሚውሉ የማዳበሪያ በመንግስት በኩል አለመቅቡንና እጥረቱ እንዳለ ያጋርናቸው አርሶ አደሮች አስረድተዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ከነበረው በማዳበሪያ ላይ የዋጋ ጭማሪ መደረጉንና ጫና ማድረሱን ተናግረዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበከር ሀሊፋ ለግብርና የሚሆኑ የግብአት እጥረት በተቋም ደረጃ እንዳጋጠማቸው ለዲዳቢሊው አብራርተዋል፡፡ ለአርሶ አደሩ ለማከፋፈል  በክልሉ መንግስት የቀረቡ ማዳበሪያም 40 ከመቶው ብቻ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ የዋጋ ጭማሪውም የተከሰተው በሀገር አቀፍ ደረጃ መሆኑን አክለዋል፡፡ 

ባለፈው ዓመት በክልሉ በምርት ለመሸፈን ከታቀደው መሬት መካከል በጸጥታ ችግር ምክንያት ግመሽ ያህሉ ብቻ የለማ ሲሆን 31 ሚለዮን ኩንታል በክልል ደረጃ ለመሰብሰብ ታቅዶ እንደበር ከቢሮው የተገኜ መረጃ ያመለክታል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግማሽ ሚሊዩን ያህል የሚሆነው ህዝብ ከዚህ ቀደም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው እንደሚገኙና ወደ ቀዬአቸው አለመመለሳቸውን መዘገባችንም ይታወሳል፡፡

ነጋሣ ደሳለኝ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ