1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከኢሰመኮ እና ከሲቪል ማህበረሰብ ም/ቤት የቀረበ የሰላም ጥሪ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 24 2014

ኢሰመኮ እና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁሉም ወገኖች ግጭቱን እንዲያቆሙና ውይይታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀረቡ። ኢሰመኮ በትጥቅ ግጭቶች የተጎዱትን ሰላማዊ ዜጎች ህይወት፣ ደህንነት፣ አካላዊና ሞራላዊ ክብርን ለመጠበቅ በግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች ግዴታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

https://p.dw.com/p/4GEXF
Äthiopien | EHRC-Vizekommissar Rakeb Mele und Kollegen
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

በትጥቅ ትግሉ የተጎዱ አካላዊና ሞራላዊ ክብርን ለመጠበቅ በግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች ግዴታቸውን እንዲወጡ

ከኢሰመኮና ከሲቪል ማህበረሰብ ም/ቤት የቀረበ የሰላም ጥሪ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ሰሜን ኢትዮጵያ ላይ ዳግም የተጀመረውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁሉም ወገኖች ግጭቱን እንዲያቆሙ እና ውይይታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀረቡ። ኢሰመኮ በትጥቅ ግጭቶች የተጎዱትን ሰላማዊ ዜጎች ህይወት፣ ደህንነት፣ አካላዊ እና ሞራላዊ ክብርን ለመጠበቅ ሁሉም በግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች ግዴታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል። የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በበኩሉ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እጅግ እንዳሳሰበው ገልጾ ግጭቱ እንዲረጋጋ እና የተጀመረው የሰላም ሂደት በአስቸኳይ እንዲቀጥል ጠይቃል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሰላም ጥረት እንዲቀጥል በጠየቀበት መግለጫው ሁሉም ወገኖች በግጭቱ ተጋላጭ የሆኑ ሰላማዊ ዜጎችን ሕይወት፣ ደኅንነት፣ አካላዊ እና ሞራላዊ ልዕልና ብሎም ክብራቸውን የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብሏል።

ዜጎች ከቅርብ ጊዜ ሰቆቃ ሳይላቀቁ ቤተሰቦቻቸውን እና የሚወዷቸውን አጥተው፤ አስፈላጊ አገልግሎቶች ተነፍገው ፍትሕ እና ፈውስን ይጠብቃሉ ያለው ኢሰመኮ በአፋር እና በአማራ ክልሎች ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ከተፈፀመባቸው ሰዎች ጋር በመምከር እንዲሁም በትግራይ ያለውን ሁኔታ በርቀት በመከታተል ደረስሁበት ባለው ግኝት በእነዚህ ክልሎች ውስጥ ያለው ህዝብ የተራዘመ የጦርነት ፍርሃት ውስጥ እንደሚኖር ያሳያል።

ሰላማዊ ዜጎች ቀዳሚ ፍላጎታቸው ሰላምና ደህንነት መሆኑንም እንደገለፁለትና "በግጭቱ ውስጥ ያሉ አካላት በእውነት ወደ ውይይት ከገቡ እና የባህል እና የሃይማኖት መሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ የሀገር ውስጥ ተዋናዮችእና ሴቶች ከተሳተፉ" ሰላም እና እርቅ ይወርዳ ብለው ያምናሉ። ሲል ጠቅሷል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ መገናኛ ብዙኃን፣ የባህል እና የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ፣ ውይይቶችን በማመቻቸት እና በተጎዱ ክልሎች ውስጥ ያሉ ሁሉም ሲቪሎች ሰብአዊ መብቶቻቸው እንዲጠበቁ እንዲያግዙባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ከዚህ በፊት በተከሰተው ግጭት የደረሰውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ዳግም እንዳይከሰት ለማሳሳበብ ይህ መግልጫ መውጣቱን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በበበኩሉ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው የትጥቅ ትግል እንዲረጋጋ እና የተጀመረው የሰላም ሂደት በአስቸኳይ እንዲቀጥል ሲል ጠይቋል።

ከዚህ በፊት የተፈጠረው የትጥቅ ግጭት ተነግሮ የማያልቅ የሰው ልጅ ስቃይ እና ለከፍተኛ የመሰረተ ልማቶች መውደም ምክንያት መሆኑን ያስታወሰው ምክር ቤቱ አሁን ዳግም የተቀሰቀሰው የትጥቅ ግጭት እንዳይባባስ አስፈላጊው ሁሉ እንዲደረግ ብሎም አስቸኳይ የሰብዓዊ ተኩስ አቁሙ መከበር  እንዲቀጥል ጠይቋል።

አለመግባባቶች በፖለቲካዊ ውይይት መፍታት ይገባል ያለው ይሄው ተቋም ሀገሪቱንና ዜጎቿን ከተጨርማሪ ጥፋት ለመታደግ የሰላም ሂደቱ በቅን ልቦና እንዲካሄድ ጠይቋል። የአፍሪካ ሕብረት የፌደራል መንግስትን እና ሕወሓትን የማደራደር ሚናውን በእጥፍ በማሳደግ ሰላማዊ መፍትሔ ላይ እንዲደረስ ጥሪ አቅርቧል። የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ አሁን ዳግም የተጀመረው ግጭት ዐቃቤ ሕግ ከዚህ በፊት ኮሚሽኑ ባደረገው በጦርነት የደረሱ ጥፋቶች ምርመራ ተጠያቂነትን ለማስፈን ሂደት ላይ ባለበት መሆኑንም ገልጸዋል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ