1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢሰመኮ ዓመታዊ መግለጫ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 22 2015

የኮቪድ ወረርሽኝ፣ ድርቅ፣ ጦርነትና ግጭት በሴቶችና ሕፃናት መሰረታዊ መብቶች ጥበቃ ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደራቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጉዳዩ ላይ ያወጣው አመታዊ የምርመራ ውጤት ይፋ አደረገ።

https://p.dw.com/p/4Iv3R
Äthiopien l Gebäude Ethiopian Human Rights Commission( EHRC)
ምስል Solomon Muchie/DW

ከ20 ሺህ በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል

የኮቪድ ወረርሽኝ፣ ድርቅ፣ ጦርነትና ግጭት በሴቶችና ሕፃናት መሰረታዊ መብቶች ጥበቃ ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደራቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጉዳዩ ላይ ያወጣው አመታዊ የምርመራ ውጤት ይፋ አደረገ።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ያወጣው የሴቶችና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፓርት በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎችም በተነሱ ኃይል የቀላቀሉ ግጭቶች ምክንያት የሕፃናት በሕይወት የመኖር፣ ከጥቃት የመጠበቅ፣ ድጋፍና ፍትሕ የማግኘት፣ የትምህርትና የጤና መብቶቻቸው ተጥሰዋል ብሏል።

ከግጭቶቹ ጋር በተያያዘ ሕፃናት የሞት፣ የአካል እና የሥነ-ልቦና ጉዳቶች የደረሱባቸው ሲሆን ከቤተሰብ በመነጠልና በመፈናቀል የተነሳ ለአሳሳቢ ችግሮችና የመብት ጥሰቶች ተጋልጠው ይገኛሉም ተብሏል።

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ በርካታ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃይ ሕፃናት ለከፍተኛ የምግብ እና የውኃ እጥረት፣ ለበሽታ እና ወረርሽኝ፣ ለጉልበት ብዝበዛ እና ለሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ለልመና እና ለወሲባዊ ጥቃቶች ተጋላጭ መሆናቸውም በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ