1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከፋኖ ቃል አቀባይ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

ነጋሽ መሐመድ
ዓርብ፣ መስከረም 11 2016

ራሱን የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ ብሎ የሚጠራዉ ቡድን ከኢትዮጵያ መከላከያ ጦር ጋር በገጠመዉ ዉጊያ ሽንፈት እንዳልገጠመዉ አስታወቀ። ባጭሩ ፋኖ በሚል ስያሜ የሚጠራዉ ቡድን ቃል አቀባይ እንደሆኑ የነገሩን ግለሰብ በተለይ ከዶቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ታጣቂዎቹ በህዝብ ላይ ያደርሱታል የሚባለዉን ዘረፋና በደል ሙሉ በሙሉ አስተባብለዋል።

https://p.dw.com/p/4WezK
Äthiopien | Kämpfer der Fano-Miliz in Lalibela in der nördlichen Amhara-Region
ምስል Solan Kolli/AFP/Getty Images

ከፋኖ ቃል አቀባይ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

 

በአማራ ክልል የሸመቀዉ ራሱን የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ ብሎ የሚጠራዉ ቡድን ከኢትዮጵያ መከላከያ ጦር ጋር በገጠመዉ ዉጊያ ሽንፈት እንዳልገጠመዉ አስታወቀ።የጦርነት ቀናት ውጥረት እና ሥጋት ፣ የዓይን ምስክር ከደብረ ታቦር ባጭሩ ፋኖ በሚል ስያሜ የሚጠራዉ ቡድን ቃል አቀባይ እንደሆኑ የነገሩን ግለሰብ በተለይ ከዶቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ  ታጣቂዎቹ በህዝብ ላይ ያደርሱታል የሚባለዉን ዘረፋና በደል ሙሉ በሙሉ አስተባብለዋል።ስማቸዉ እንዲሸሸግላቸዉ የጠየቁት ቃል አቀባይ፣ ቡድናቸዉ የጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድን መንግስት በትጥቅ ትግል አስወግዶ የመንግስትነት ሥልጣኑን ለሕዝብ የማስረከብ አላማ እንዳለዉ አስታዉቀዋል።ጅምላ እስር፤ ተመድ፤ ብሪክስና የኑሮ ውድነትይሁንና ቡድኑ ያቀረበዉ አንድ ቅድመ ሁኔታ ከተሞላ ከመንግስት ጋር የመደራደርን ጉዳይ እንደሚያስብበት አስታዉቀዋል።ፋኖ የፖለቲካ ፓርቲ እንደሌለዉ አስታዉቀዋልም።ሙሉ ቃለ ምልልሱን ያድምጡ።በሰሜን ሸዋ ደራ የተከሰተው ግጭት

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ