1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከሰሜን ምዕራብ ትግራይ ብዙ ሰዎች ተፈናቀሉ

ዓርብ፣ ጥቅምት 11 2015

እንደ የትግራይ ክልላዊ መንግስት ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ መረጃ ከሽረ ጨምሮ ከአጠቃላይ የሰሜን ምዕራብ ትግራይ አከባቢዎች ጦርነቱ ሽሽት ከ470 ሺህ በላይ ህዝብ ከነሐሴ አጋማሽ ወዲህ ተፈናቅሎ ወደ ተለያዩ አካባቢ ተሰዷል

https://p.dw.com/p/4IWqp
Äthiopien Flüchtlingsunterkünfte Mekele
ምስል Million Haileselassie/DW

«ከነሐሰ አጋማሽ በኋላ የተፈናቀለዉ ሕዝብ ከ470 ሺሕ በልጧል» ትግራይ ክልል

 

የኢትዮጵያ መንግስትና ተባባሪዎቹ ኃይላት ከህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ታጣቂዎች ጋር ከፍተኛ ዉጊያ ከሚያደርጉባቸዉ ከሰሜን ምዕራብ ትግራይ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ መፈናቀሉን የትግራይ የማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።ቢሮዉ እንዳስታወቀዉ የኢትዮጵያ መንግስትና የተባባሪዎቹ ኃይላት  ባለፈዉ ሰኞ ከተቆጣጠራት ከሽረና አካባቢዉ ከ470ሺሕ በላይ ሕዝብ ተፈናቅሏል።ዉጊያዉን ሸሽተዉ መቀሌ መግባት ከቻሉ ተፈናቃዮች አንዳዶቹ እንዳሉት የመጓጓዢያ ዋጋ አለቅጥ በመናሩ ለአንድ ሰዉ እስከ 7 ሺሕ ብር ለመክፈል ተገድደዋል።
ሰሞኑን በሽረ ጨምሮ በተለያዩ የሰሜን ምዕራብ አካባቢዎች ጦርነቱ መቀጠሉ ተከትሎ በርካቶች ከከተማው እና አካባቢው ተፈናቅለው ወደ መቐለ እና ሌሎች የትግራይ ከተሞች እየደረሱ ይገኛሉ። በመቐለ ያነጋገርናቸው ከሽረ ተፈናቅለው የመጡ ዜጎች ጦርነቱ ሽሽት ለአንድ ሰው እስከ 7 ሺህ ብር ለትራንስፖርት በመክፈል ከሽረ ወደ መቐለ መምጣታቸው ገልፀውልናል። የትግራይ ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ በተለይም ከኤርትራ ጋር ከሚዋሰኑ አካባቢዎች በየቀኑ በርካታ ህዝብ ቅየው ለቆ እየተሰደደ መሆኑ ተከትሎ የተፈናቃዩ ቁጥር እየጨመረ ስለመሆኑ ይገልፃል። የትግራዩ ጦርነት እና የነዋሪዎች የሰላም ጥሪ

ነሐሴ አጋማሽ ጦርነቱ ዳግም ከተቀሰቀሰ እና የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሀይሎች በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በኩል እያደረጉት ካለ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ እንደአዲስ እየተፈናቀለ ይገኛል። ሰሞኑን በሽረ ጨምሮ በተለያዩ የሰሜን ምዕራብ አካባቢዎች ጦርነቱ መቀጠሉ ተከትሎ በርካቶች ከሽረ እና አካባቢው ተፈናቅለው ወደ መቐለ እና ሌሎች የትግራይ ከተሞች እየደረሱ ነው። በመቐለ ያነጋገርናቸው ከሽረ ተፈናቅለው የመጡ ዜጎች ጦርነቱ ሽሽት ለአንድ ሰው እስከ 7 ሺህ ብር ለትራንስፖርት በመክፈል ከሽረ ወደ መቐለ መምጣታቸው ገልፀውልናል። እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ ገለፃ ከረዥም የጦርነት ቀናት በኃላ ሰኞ እለት "የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግስት ጦሮች" ወደ ከተማዋ የገቡ ሲሆን፣ የገባው ጦር በመስጋት በርካቶች እየተፈናቀሉ መሆኑ ይናገራሉ። እሁድ እለት ከሽረ ተነስታ ከሁለት ህፃናት ልጆችዋ ጋር መቐለ የደረሰችው ተበርህ የተባለች እናት፣ ለቀናት በሽረ ከተማ ላይ ይፈፀም የነበረ የአየር ላይ ድብደባ፣

Äthiopien | IDP-Zentrum in Mekelle | Region Tigray
በመቀሌ ከተማ የሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያምስል Million Hailessilasie/DW

የመድፍና ሌሎች ከባድ መሳርያዎች ጥቃት በመስጋት ቅየዋ ለቃ እንደተፈናቀለች ትገልፃለች። ራያ እና ሽረ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መያዛቸውን የክልሉ መንግሥት አረጋገጠ

እንደ የትግራይ ክልላዊ መንግስት ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ መረጃ ከሽረ ጨምሮ ከአጠቃላይ የሰሜን ምዕራብ ትግራይ አከባቢዎች ጦርነቱ ሽሽት ከ470 ሺህ በላይ ህዝብ ከነሐሴ አጋማሽ ወዲህ ተፈናቅሎ ወደ ተለያዩ አካባቢ ተሰዷል። ከእነዚህ ተፈናቃዮች ጥቂት የማይባሉት በሁለት ዓመቱ ጦርነት ምክንያት ዳግም የተፈናቀሉ ናቸው ተብሏል። በትግራይ ሰራተኛ እና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሕብረተሰብ ችግሮች ጉዳይ አጥኚ አቶ አደራጀው ሹሻይ "ከኤርትራ ጋር ከሚዋሰኑ እና ጦርነት እየቀጠለባቸው ካሉ ሌሎች አካባቢዎች አሁንም በየቀኑ ዜጎች በከፍተኛ መጠን እየተፈናቀሉ ነው" ሲሉ ለዶቼቬለ ገልፀዋል። ተፈናቃዮቹ እና የትግራይ ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለነዚህ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ተፈናቃዮች እስካሁን የተደረገላቸው እርዳታ የለም ብለዋል።

ለበርካቶች ሞት፣ ጉዳት እና መፈናቀል ምክንያት የሆነው ጦርነት አሁንም ተባብሶ በሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ደቡብ ትግራይ በኩል እየቀጠለ ስለመሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ